Logo
News Photo

አምሬፍ ሔልዝ አፍሪካ የተሰኘ አለምአቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት አጠቃላይ ግምቱ ግማሽ ሚሊየን ብር የሚጠጋ የተለያዩ የህክምና መስጫ እና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ከፍታ/የተቀናጀ የወጣቶች ተግባር/ (Integeration Youth Activity) ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩ.ኤስ .ኤይድ (USAID) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአምሬፍ ሔልዝ አፍሪካ እና በአጋሮቹ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር በቅንጅት የሚተገበር ፕሮጀክት ነው፡፡ 

ግብረሰናይ ድርጅቱ ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ወጪያቸው 540 ሺህ ብር የሆኑ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን እና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልክ አበርክቷል፡፡

የከፍታ ፕሮጀክት የድሬደዋ እና የሐረር ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ አንድነት አየለ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት የከፍታ ፕሮግራም በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በ17 ከተሞች ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኝና ወጣቶችን በሁሉም መስክ የላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲም በቅርብ ለተቋቋመው Youth Friendly Service and carrier development center አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ከማዕከሉ ጋር በመሆን ሰፋፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል ብለዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ግብረሰናይ ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ድርጅቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ለሚሰራቸው ስራዎች ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

Share This News

Comment