Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከJhpeigo የጤና የሰው ሃይል ማሻሻያ ፕሮግራም (HWIP) ጋር በመተባበር በክሊኒካል ትምህርት ጥራት ላይ አውደ ጥናት አካሄደ።

በአውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታል እና የጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጆች እና ፕሪሴፕተሮች ተሳትፈዋል። የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሁሴን መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል። 

ዶክተር ሁሴን በንግግራቸው የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ እውን ለማድረግ የኮሌጁን እድገት አብራርተው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራልና ማስተማሪያ ሆስፒታል በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርና ሆስፒታሉ ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት እየሰራን መሆኑን ገልፀዋል። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ተብሎ የተመደበው አንዱ የትኩረት መስክ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ሲሆን በጤና ሳይንስ የላቀ ደረጃን ለማስመዝገብ እየሰራን መሆኑን ገልፀው የጤና ባለሙያዎችን ጥራት ለማረጋገጥ ላደረጉት አስተዋፅኦ የ Jhpeigo የጤና የሰው ሃይል ማሻሻያ ፕሮግራምን (HWIP) አመስግነዋል። 

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና Jhpeigo በክሊኒካል ትምህርት ላይ የተደረገው የዳሰሳ ጥናት ከአካዳሚክ ሰራተኞች፣ ከሆስፒታል ፕሪሴተሮች እና ከተማሪዎች የተሰበሰበ መረጃ በረዳት ፕሮፌሰር ለገሰ አበራ ቀርቧል።

ጥሪ የተደረገላቸው የአርሲ ዩኒቨርሲቲ፣ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎች የክሊኒካል ማስተማር ልምዳቸው ቀርቧል።

በመጨረሻም ከተሳታፊ ተማሪዎች፣ ከሆስፒታል ፕረሲፕተሮች፣ ከሆስፒታልና ከጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጆች፣ ከዩኒቨርሲቲው ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ኃላፊዎች አስተያየት ቀርቦባቸው ክፍተቶች ተለይተው፣ የባለድርሻ አካላት ሚና፣ የሆስፒታል ፕረሲፕተሮች ሚና እና በክሊኒካል ትምህርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ላይ በግልፅ ውይይት ተደርጓል።

Share This News

Comment