Logo
News Photo

ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ዘርፍ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት፡፡

አዋርድ ድሬ የድሬደዋ ተወላጅና ወዳጅ በሆኑ በጎፈቃደኞች በድሬደዋ ባለፈው 2014 ዓ.ም የተቋቋመ የሽልማት ድርጅት ነው፡፡ ድረጅቱ በ2013 ዓ.ም የላቀ አስተዋፆኦ አበርከተዋል ላላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች እውቅና በመስጠት እንቅስቃሴውን የጀመረ የሽልማት ድርጅት መሆኑን ትናንት ምሽት በድሬደዋ ራስ ሆቴል በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ ባለፈው ዓመት በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አስተዋፆኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ድርጅቶች የአውቅና ሽልማትን ያበረከተ ሲሆን በማኅበራዊ ዘርፍም የላቀ አስተዋፆኦ በማበርከት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተሸላሚ መሆን ችሏል ፡፡
በእውቅና የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ሽልማቱን ከእለቱ የክብር እንግዳ የተረከቡት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግልት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ሽልማቱ ዩኒቨርሲቲው በማኅበራዊው ዘርፍ የጀመረውን አበርክቶ ከቀድሞ በበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥርለት ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
በድሬደዋ ራስ ሆቴል በተዘጋጀው የአዋርድ ድሬ የሽልማት ፕሮግራም ላይ የድሬደዋ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የቀድሞ ከንቲባ የተከበሩ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በትምህርት ፣ በህክምና፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በኪነ-ጥበቡ እና በአጠቃላይ ዘርፍ በ2014 ዓ.ም የላቀ አስዋፆኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ድረጅቶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Share This News

Comment