Logo
News Photo

በምስራቅ ክላስተር ለሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የታሪክ ትምህርትን(Ethiopian History and the horn) ለሚሰጡ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

ከሀረማያ ፣ ከድሬደዋ ፣ ቀብሪዳህር ፣ኦዳቡልቱም  ከሰመራ እና ከጂጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች  ለተወጣጡ የጋራ ኮርሶችን ለሚሰጡ የታሪክ መምህራን በቀጣይ ትምህርቱ በሚሰጥብት ሁኔታ ላይ ግንዛቤ የሚያገኙበት ገለፃ የተደረገ ሲሆን በመድረኩ ላይ የተገኙት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡

ከእነዚህ ሥራዎች መካከልም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ስራ እየተሰራ ሲሆን የትምህርት ጥራት ከማስጠበቅ አንፃርም የታሪክ ትምህርትን(Ethiopian History and the horn) በሚፈለገው አግባብ ለተማሪዎች መስጠት እንዲቻል ትልቅ ድርሻ የሚወስዱት መምህራን እንደመሆናቸው የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጡ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ለአንድ ቀን በቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪዎች ማኅበር የመጡት ዶ/ር መሐመድ ሀሰን ገለፃና ማብራሪያውን ሰጥተዋል፡

Share This News

Comment