Logo
News Photo

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የተሰራው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ማስተዳደሪያ ሲስተም የአፕሊኬሽን ሶፍትዌር ከኢትዮጲያ አእምራዊ ንብርት ባለስልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት አገኘ፡፡

በዩኒቨርሲቲያችን መምህራን በሆኑት አንድነት አሰፋ፣ ጌትነት ቶለሳና ፀጋ እንደሻው በልፅጎ በድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አገልግሎት ላይ የዋለው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ማስተዳደሪያ ሲስተም የአፕሊኬሽን ሶፍትዌር የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የሚያስገኙ ስራዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘ ሲሆን ይህ የፈጠራ ስራ በዪቨርሲቲው መምህራኖች ከበለፀጉት የተለያዩ ሶፍትዌሮች የምዝገባ ምስክር ወረቀት በማስገኘት  የመጀመሪያው በመሆኑ በዚህ ስራ ለተሳተፉት መምህራን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን በማለት ዩኒቨርሲቲው የተሰማውን ደስታ ይገልፃል፡፡  

ዩኒቨርሰቲው በቀጣይ መምህራኖች እና ተመራማሪዎች የሚሰሩትን የፈጠራ  እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለተጠቃሚዎች  በማሸጋገር የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱ ለማስቻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አትኩሮ የሚሰራ እና ተገቢውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃል፡፡

Share This News

Comment