Logo
News Photo

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት አራት ቀናት

"በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል ርዕስ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አመራሮች ፣ መምህራን እና በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር አመራሮች ላለፋት ሁለት ቀን በሁለተኛው ዙር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ  መምህራን እንደገለፀት በነበራቸው ቆይታ አገር ያለችብትን ወቅታዊ ሁኔታ በስፋትና በጥልቀት  ገለፃና ማብራሪያ የተደረገላቸው በመሆኑ ከቀድሞ በበለጠ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መደረጉን ተናግረዋል፡፡

"አገር በምትፈልገን መስክ  ሁሉ የአቅማችን ለማበርክት ዝግጁ ነን ያሉት " ምሁራኑ በተለይም የአገራችን የኢንደስትሪ ኮሪደር ሆና የተመረጠችው ድሬደዋ የሰነቀችውን ርዕይ ማሳካት እንድትችል በመማር ማስተማሩ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት አንፃር  በጥናትና ምርምር ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች  በማበርክት በሀገር ግንባታው ሂደት የበኩላችን  ሚና ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት በተለይ የመምህራኑ ዋነኛ ችግር የሆኑትን የገቢ አቅም ዝቅተኛ መሆንን፣የመኖሪያ ቤት ችግር እና ጥቅማ ጥቅማቸው እንዲከበር የበኩሉን እንዲወጣ በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

ይህን የውይይት መድረክ በዋና አወያይነት ሲመሩ የነበሩት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ምሁራን ለሀገር ግንባታው ሂደት ስኬታማነት ሊኖራቸው የሚችለው ሚና ከፍተኛ ድርሻ መሆኑን ተገንዝበው በዚሁ አግባብ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም በአሁኑ ሰዓት የአካባቢያችን ስጋት የሆነውን  አክራሪነትንና ፅንፈኝነትን በመከላከል ረገድ  ምሁራን  ጥናትና ምርምርን መሠረት ያደረጉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን መጠቆም የሚችሉ ስራዎችን በማበርክት የበኩላቸውን ይወጡ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው " ዛሬ ላይ በአንፃራዊነትም ቢሆን የሰላም አየር መተንፈስ የቻልነው በየግንባሩ ተሰልፈው ወድ ህይወታቸውን ሳይሰስቱ በመሰዋትንት ባቀረቡ  በጀግኖች ወንድሞቻችንና እህቶቻቸን ተጋድሎ የመጣ መሆኑን ግንዛቤ ወስደን አገራችን በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው እንቅስቃሴ  ውስጥ ሁላችንም ከቀድሞ በበለጠ ርብርባችን አጠናክረን መቀጠል ሀገራዊ ኃላፊነታችን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

"የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አስተዳደሩ በሁሉም መስክ በጀመራቸው የልማትና የእድግት እንቅስቃሴዎች ላይ  እያደረጉት ላለው እገዛ ትልቅ ቦታ ይሰጣል" ያሉት ክቡር ክንቲባው ምሁራኑ  በተለይ ከመኖሪያ ቤት ጋር በተያያዘ ላነሱት ጥያቄ በቀጣይ አስተዳደሩ በተቻለው አቅም የመኖሪያ ቤት መስሪያ የሚያገኙበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተቀራርቦ በመስራት ጥረት የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው መምህራኖቹ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በተያያዘ ላነሷቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

"በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል ርዕስ ካለፈው አርብ ታህሳስ 21/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር ሲደረግ በነበረው የውይይት መደረክ ላይ ቁጥራቸው 700 በላይ የሆኑ  የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አመራሮች ፣ መምህራን እና በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር አመራሮች  ተሳታፊ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment