Logo
News Photo

በድሬደዋ ከተማ ጎዳና ላይ የሚገኙና እድሚያቸው ለስራ የደረሱ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና በSOS የሐረር የህጻናት ማሳደጊያ መንደር መካከል ተፈረመ፡፡

የጋራ የስምነት ሰነዱ በቀጣይ ሁለቱ አካላት በጋራ በመሆን ጎዳና ላይ የሚገኙና እድሚያቸው ለስራ የደረሱ ዜጎችን ህይወት ማሻሻልን ዋነኛ ዓላማ ያደረጉ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንተርፕራይዝ የሚመሰርቱ ሲሆን እነዚህም ተቋማት ቀስ በቀስ እየሰፉ በፕሮጀክቱ የሚታቀፉትን ቁጥር እያሳደጉ የሚሄዱ ናቸው፡፡
የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እና የSOS ሐረር የህፃናት ማሳደጊያ መንደር ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንዱዓለም ጌታቸው ናቸው፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት የጋራ የስምምነት ሰነዱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአጋር አካላት በጋራ በመሆን የምንሰራቸውን ፕሮጀክቶች ማሳደግ መቻላችን የሚያሳይ ከመሆኑ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው በማኅበራዊ አገልግሎት ተልዕኮውን በብዛትና በጥራት በእጥፍ ለማሳደግ የያዘውን እቅድ ስኬታማ እንዲሆን ሰፊ እድልን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
የSOS ሐረር የህፃናት ማሳደጊያ መንደር ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አንዱኣለም ጌታቸው በበኩላቸው ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ተባብረው ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ለስራ የደረሱና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጀ ላይ የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ችግሮችን በጥናት በመለየት በአጭር ጊዜወ ውስጥ ለመቅረፍና የተሻለ ህይወት መምራት የሚችሉብትን እድል ለመፍጠር የያዙትን እቅድ ማሳካት እንዲችሉ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በዚሁ የጋራ የመግባቢያ የስምምንት ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬደዋ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በበኩላቸው ሁለቱ አካላት ለስራ የረደሱ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኑሯቸውን በጎዳና ላይ በማድረግ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖቻችን ህይወት ለማሻሻል በጋራ ሆነው የጀመሩትን እንቅስቃሴ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው በማለት ጥሪያቸውን አቅርበው ለፕሮጀክቱ ስኬትም ቢሯቸው አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በመጨረሻም በጋራ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሰነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደምን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የSOS ሐረር ህፃናት ማሳደጊያ መንደር ፕሮግራም ከፍተኛ ኃላፊዎችና ፕሮግራም አስተባባሪዎች እንዲሁም የድሬደዋ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴንን ጨምሮ የተለያዩ ተቋም ባለሞያዎችና የስራ ክፍል ኃላፊዎች የSOS የሐረር ህጻናት መንደር በድሬደዋ ቴክኒክና ሞያኮሌጅ በጨርቃጨርቅና የአልባሳት ስፌት ስራ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ እና ከዚህ ቀደም በጎዳ ላይ ለተለያዩ አደጋዎች አጋላጭ በሆነ ሁኔታ ህይወታቸውን ሲመሩ የነበሩ ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶች ስልጠና እየወሰዱበት ያለውን ስልጠና ማዕከል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

Share This News

Comment