Logo
News Photo

ዛሬ “በCOVID-19 ወቅት አስፈላጊ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን ቀጣይነት ማረጋገጥ” በሚል ርዕስ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) grant የተደረገለት የፕሮጀክት ግምገማ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።

በCOVID-19 ወቅት አስፈላጊ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን ቀጣይነት ማረጋገጥ” በሚል ርዕስ በተካሄደው ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሁሴን መሀመድ ናቸው። ፕሮጀክቱ ከድሬዳዋ   አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር እና በአለም ጤና ድርጅት (WHO) የገንዘብ ድጋፍ እየተካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል። 

ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፎች (Phase-I and-II) ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰዋል። የCOVID-19 በአስፈላጊ የጤና አገልግሎት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመገምገም የመጀመርያው ምዕራፍ ጥናት ከድሬዳዋ   አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ተካሂዷል። በግኝቶቹ ላይ በመመስረት አሁን  በትብብር ተግባራዊ እያደርን እንገኛለንም ብለዋል። የሂደቱ ሪፖርት እና በፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን በ ረ/ፕ አብዱረዛቅ አደም ቀርቧል። በተሳታፊዎች የውይይት ነጥቦች ተነስተዋል።ከ3 ድርጅቶች የተውጣጡ ፓናልስት፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮች ለውይይት መድረኩን መርተዋል።ወደፊትም የጤናን ችግር ለመፍታት በጋራ ሁለቱም ተቋም መስራት እንዳለባቸውም ተጠቅሰዋል። 

በመጨረሻም የመዝጊያ ንግግር የደረጉት በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ  ድሬደዋ ዩኒሸርሲቲን ላበረከተው አሰተዋጾ በማመስገን በጋራ ለመስራት ያለውን ፍላጎት አጽኖት ሰጥቶ ተናግረዋል። 

Share This News

Comment