Logo
News Photo

ሀገር በቀል እውቀቶችን ከሳይንስ ጋር በማቀናጀት ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፕቴሽናል  ኮሌጅ እንደ ኮሌጅ ለ3ኛ ዙር ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ "ሀገር በቀል አውቀቶችን ከሳይንስ ጋር በማቀናጀት ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ" የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በኮንፈረንሱ ላይ ስምንት የተለያዩ የምርምር ስራዎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የኮንፈረንሱን ተሳታፊዎች እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግልት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ካለፈው ዓመት ወዲህ በዩኒቨርሲቲው የተሻለ የምርምር የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ለተመራማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር  ውጤታማ የሆኑ ስራዎች መሰራት መቻሉን ጠቅሰው  የተሰሩት የምርምር ስራዎችም ወደ ማኅበረሰቡ መውረድ እንዲቻል በሰፊው እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። 


በዚሁ ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች  ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ባስተላለፋት መልዕከልት ሀገር በቀል እውቀትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማቀናጀት የአገራችን ህዝብ ከድህንትና ከኋላቀርንት የሚያላቅቁ የምርምር ስራዎችን መስራት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይጠበቃል ፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲም በተለይም የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን በተደረገው ልየታ መሰረት የካበተ ተግባራዊ አውቀት ያላቸው ተማሪዎችን በማፍራት ለአገር ዘላቂ ልማት መረጋገጥ መምጣት ትልቅ ድርሻ ማበርክት የሚችሉ ብቁ ባለሞያዎችን በማፍራት በኩል አሁን ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በላቀ ደረጃ ለመከወን  እቅድ ተነድፎ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ሲሉ ዶ/ር መገርሳ ተናግረዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ በመገኘት ቁልፍ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ያለምፀሐይ መኮንን በበኩላቸው ሙሁራኖች የምርምር ልምዳቸውን በማዳበር በተለይም በአካባቢያቸው ያሉ ሀገር በቀል እውቀቶች ላይ ትኩረት በማድረግ አገር ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ከድህነት መላቀቅ እንድትችል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ለአንድ ቀን በቆየውና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜ በኮሌጅ ደረጃ ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ በተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፕቴሽናል  ኮሌጅ  የተዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ 8 የምርምር ስራዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ ምሁራን ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው መምህራን የሚሰሯቸው የምርምር ስራዎች ለማህበረሰቡ ለውጥ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያድርጉ መሆን እንዳለባቸውና እና መሰል የምርምር መድረኮችንም በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል። ተሳታፊዎቹ  በዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በኩል የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Share This News

Comment