Logo
News Photo

አስደሳች ዜና ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ጥር 30/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የሶስት ተመራማሪ መምህራን እድገት አጽድቋል፡፡ የሴኔት አባላቱ ባደረጉት ስብሰባ በኮሌጅና በSPARC የፀደቁ የመምህር ደረጃ እድገትን አስመልክቶ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ እና የተፈጥሮና ኮሚፒዩተሸናል ሳይንስ ኮሌጅ ወደ ተባባሪ ፕሮፌሰር ደረጃ እድገት እንድፀድቅላቸው ለሴኔት መማክርት አባላት አቅርቧል። በዚህ መሰረት የመማክርት ጉባዔ አባላት በየደረጃው ከሚመለከታቸው ክፍሎች ተገምግሞ በቀረበዉ መሰረት ለሶስት ወጣት ተመራማሪዎች የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ደረጃ እድገት አፅድቋል፡፡ 

1. Dr. Mohammed Kasso Geda- Associate Professor of Ecology and Systematic Zoology 

2. Dr. Daniel Mamo G/Tsadik - Associate Professor of Educational Leadership & Policy

3. Dr. Wondeferaw Dejene Chala- Associate Professor of Curriculum and Instruction 

ዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎቹ ባገኙት የደረጃ ዕድገት እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

Share This News

Comment