Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ያስተማራቸውን 155 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬው እለት ለ6ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው 155 ተማሪዎች መካከል 132 በሜዲሲን፣ በሚድዋይፈሪ ፣ በነርሲንግ፣ በአንስቴዢያ፣ በሳይካትሪ ነርሲንግ እና በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ በቅድም ምራቃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን 23 ደግሞ በአጠቃላይ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች መሆናቸውን በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒንስትር ሚኒስቴር ዲዔታ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፋት መልዕክት ላይ እንዳመለከቱት ተመራቂ ተማሪዎች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ህዝባቸውን በታማኝንት ማገልግል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተለይም በጤና አገልግልት እጦት ለሞትና ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭ የሆነውን ማህበረሰብ በማገልገል የበኩላቸውን ኃላፊነት ይወጡ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡


የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤናው ዘርፍ ብቁና የሰለጠኑ ባላሞያዎችን ከማፍራት ጎን ለጎን በማህበረሰብ አገልግሎት እንቅስቃሴው በድሬደዋና በአካባቢው ለሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል የተለያዩ ተጠቃሽ የሆኑ ተግባራትን በማካናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው እነዚህም ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በከፍተኛ ውጤት ለተመረቁ ተመራቂ ተማሪዎች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Share This News

Comment