Logo
News Photo

በአዲስ መልክ የተደራጀው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሲቪል ምህንድስና ሀይድሮሊክ ቤተ-ሙከራ (ላብራቶሪ) ተመርቆ ለአገልግልት ክፍት ሆነ፡፡

ላብራቶሪውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደምና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች መርቀው የከፈቱት ሲሆን በአዲስ መልክ የተደረጃውን ላብራቶሪን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳች ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንዳሉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአፕላድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ ለተማሪዎች የሚሰጣቸው ትምህርቶችም በይበልጥ ተግባር ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ የሚያደርጉባቸው ቤተ-ሙከራዎችን የማስፋፋትና የማደረጀት ስራ ከዩኒቨርሲቲተው ይጠበቃል፡፡
በዛሬው እለትም ለምረቃ የበቃው የሲቪል ምህንድስና ሀይድሮሊክ ቤተ-ሙከራ በራስ አቅም ባለን ውስን ሀብት በርካታ ስራዎችን መስራት እንደምንችል የሚያረጋግጥል ነው ያሉት ዶ/ር መገርሳ በተለይ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ ለማድረግ ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንድስትሪዎች በመሄድ ይወጣ የነበረውን ጊዜን ከማዳንና ወጪ ከመቆጠብ አንፃር ያለው የሚጫወተው ሚና የላቀ በመሆኑ የተሰራው ስራ እጅግ የሚበረታታታና መስፋት ያለበት ነው ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ገዳፋይ በበኩላቸው የሲቪል ምህንድስና የሀይድሮሊክ ቤተ-ሙከራን ያለ ምንም ተጨማሪ ወጪ በዩኒቨርሲቲው ያለን ሃብት ብቻ ተጠቅሞ አደራጅት ለአገልግልት ማብቃት የተቻለበት ስራ ለሌሎች አርአያ የሚሆንና በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ የተቀሩት የትምህርት ክፍሎችም እንደ መልካም ተሞክሮ ወስደውት ሊተገብሩት የሚገባ ነው በማለት አስገንዝበዋል፡፡
በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክትር የሆኑት አቶ ጌቱ ግርማ በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በሲቪል ምህንድስና ሀይድሮሊክ ላብራቶሪ የማደራጀት ስራን በሌሎች የትምህርት ክፍሎች የማስፋትና የቤተ-ሙከራዎችን በዘመናዊ መንገድ የማደራጀት ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በንግግራቸው ላይ አመላክተው ይህን ስራ እንዲሳካ ላደረጉት መምህራንና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጆኦ .ቴክኒካል ፣ ውኃና አካባቢ ምህንድስና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆኑት አቶ ብርሀኑ ተክሉ የቤተ-ሙከራውን እንደ አዲስ ለማደራጀት ከመነሻው ጀምሮ የተሰሩትን ስራዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በዚህ መሠረትም ላብራቶሪው በዘመናዊ መንገድ ለማደራጀት በካይዘን መርህ ስራዎቹ መሰራታቸውን እና በውስጡም የላብራቶሪ ቴክኒሻኖች ቢሮ፣ የንድፍ ሀሳብ መማሪያ ክፍል ፣የተግባር መማሪያ ቦታ፣የገላ መታጠቢያ ክፍል ፣ የደህንነት መጠበቂ ፤ የእጅ መታጠብያ ሲንክ እና የተለያዩ አስፈላጊ አገልግልት መስጫ ግብኣቶች የተሟሉለት መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
በመጨረሻም ላብራቶሪውን በማዳራጀት ድርሻ ለነበራቸው መምህራንና ሠራተኞች ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ የእወቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡
ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-

Share This News

Comment