Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን ለሚያደርጉ ለሴት መምህራን የሜንቶርሺፕ/mentorship ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ወጣቶች ፣ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ/ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው ሁለት ቀን ስልጠና ቁጥራቸው 43 የሆኑና ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ሴት መምህራን ተሳታፊ የሆኑበት ነው፡፡
በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የም/ማ/አ/ም/ፕ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ሴት መምህራን ሴት ተማሪዎች እንዲያግዙ የሚያስችል ስረአት ለመዘርጋት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ለዚህ ደግሞ ሴት መምህራንን ለዚህ ስራ ለማዘጋጀት ታስቦ የተሰጠ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራኖች ሴት ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በዚሁ ወቅት በዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ወጣቶች ፣ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ/ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት መምህርት ይታገሱ ፍቃዱ እንዳሉት ስልጠናውን የወሰዱ ሴት መምህራን በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች ከተለያዩ ከአላማቸው ከሚያሰናክላቸው ችግሮች ተጠብቀው በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ሴት መምህራኑ እገዛና ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ ታስቦ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሴት መምህራኑ በያዝነው ዓመት መጨረሻ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በአገራችን በሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ለሴት ተፈታኝ ተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎችንና ምክር የሚያደርጉ ሲሆን በተለይም በፈተና ወቅት ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ጭንቀት ልምዳቸውን መሠረት በማድረግ እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ ፣የአጠናንና ዘዴና የግዜ አጠቃቀምን አስምልክቶ ስልጠናውን የወሰዱት ሴት መምህራኑ የተለያዩ ድጋፍና እገዛዎችን የሚያደርጉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በዘንድሮ ዓመት የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የሚደረገው እገዛም በቀጣይ ከመጀመሪያ ዓመት ጀምሮ ለሚገኙ ተማሪዎች መሰጠት እንደሚጀምርም ምምህርት ይታገሱ ፍቃዱ በስልጠናው ወቅት ባደረጉት ንግግር ላይ አመልክተዋል፡
ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-

Share This News

Comment