Logo
News Photo

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የስራ እድል ፈጠራ ለማሳደግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡ (ኢፓልኮ፣22-06-2015ዓ.ም)

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።


ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ኮርፖሬሽኑ የተፈራረሙት ስምምነት በሃገር ዉስጥ ያለውን እምቅ አቅም አውጥቶ በመጠቀም በኩል ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ገልጸው በተለይም የወጣቶችን የስራ ፈጣሪነትና የቴክኖሎጂ ሽግግር አቅም በማሳደግ በኩል ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያግዛል ብለዋል፡፡


 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም  በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችውን የእድገትና የልማት ጉዞ እቅድ ነድፎ በመስራት ላይ ከሚገኘው ኮርፖሬሽን ጋር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በመፈራረማቸው መደሰታቸውን ገልጸው አለምአቀፍ ገበያው በሚፈልገው መጠን ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል፡፡


በስምምነቱ በኮርፖሬሽኑና ዩኒቨርሲቲው መካከል ሁለንተናዊ አንድነትን በማጠናከር በስራ እድል ፈጠራ፣በጥናትና ምርምር፣በቴክኖሎጅ እና እውቀት ሽግግር ዘርፎች ሃገርን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ የሚሰሩ መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡


#IPDC

#EIC

#PMOEthiopia

                                                                   

Website - https://ipdc.gov.et/

Facebook - #IPDCEthiopia

Twitter - #@EthiopiaIpdc

Telegram - @https://t.me/ipdcofficial

LinkedIn - #ipdcethiopiaofficial

Instagram - https://lnkd.in/dsn4nG9Y

YouTube - https://lnkd.in/dJN-5


Industrial Parks Development Coorporation (https://ipdc.gov.et/)

Industrial Parks Development Coorporation Website

Share This News

Comment