Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ ለማስተማር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነቶችን በመፍጠር በሀገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱን ለመጨመር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል ከጎረቤት ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት የመማር ማስተማር እና የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለማከናወን የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናውን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

በዚህም መሰረት በሶማሌላንድ ከሚገኘው ጎሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በማድረግ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሚገኙ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች መካከል አንዱ በሆነው የስትራክቸራል ምህንድስና (Structural Engineering) ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አጠቃላይ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ከመጋቢት 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ ማስተማር ይጀምራል፡፡

በቀጣይም በሀገሪቱ የሚታየውን የምህንድስና እና ሌሎች ባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሰሩ የጎሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዲ ሁሴን እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዩች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የትግበራ ሰነዱን በተፈራረሙበት ወቅት ገልፀዋል፡፡

Share This News

Comment