Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ስነ-ስርዓት አከበረ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል ‹‹አድዋ የኢትዮጵያና የጥቁር ህዝቦች ሉዓላዊነት መገለጫ›› በሚል ከዩኒቨርሲቲው እና ከድሬዳዋ ከተማ ተጋባዥ እንግዶች ጋር በጋራ አክብሯል፡ የአድዋ ድል በዓል ስልጣኔና ዘመናዊ መሳሪያ ባልነበረበት ወቅት ነጭ ወራሪን ድል ያደረገበት የአገራችን አውራ የድል ታሪካችን ነው ያሉት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት የድል በዓሉን አስመልክቶ ንግግር አድርጓል፡፡ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ባደረጉት ንግግር አድዋ የኢትዮጵያውያን ድል ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች የድል ቀን መሆኑን አንስተው የአድዋ ጀግኖች ለአንድ ኢትዮጵያ ደም፣አጥንትና ህይወታቸውን ገብረው በአለም የናኘ ደማቅ ስም የጻፉበትና ወራሪ ምዕራባውያንን አንገት ያስደፋ ለድል በዓላችን እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን በማለት ንግግር አድርጓል፡፡

ዶ/ር መገርሳ ቃሲም አያይዘው የዛሬው ትውልድም በህዝቦች መስዋዕትነት የተገኘውን አንድነት፣ነጻነት በሠላም፣ በልማትና ፀረ- ሠላም ኃይሎችን በጽናት በመታገል የአባቶችን አደራ ለመጪው ትውልድ በክብር ሊያስተላልፍ ይገባል በማለት አባቶቻችን ዘመናዊ ትጥቅ ባልነበረባቸው ወቅት እስከ አፉ ዘመናዊ ጦር ታጥቆ የመጣውን የውጭ ወራሪ በጦርና በጎራዴ ድል ያደረገበት የአገራችን አውራ የድል ታሪካችን ነው ብሏል፡፡

ዶ/ር ተማም አወል የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት የመክፈቻ ንግግራቸውን በጣዕመ ዜማ እንዲህ ብሏል ‹‹አድዋ ዛሬና አድዋ ትናንት፤ መቼ ተነሱና የወዳደቁት፤ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፤ለዛሬ ነጸነት ላበቁን ወገኖች›› በማለት የድል በዓሉን ወኔ ቀስቃሽ በተሞላበት ንግግር አድርጓል፡፡ ዶ/ር ተማም አያይዘው የአድዋ በዓል ዓመትን ተብቆ የሚከበር በአል ሳይሆን ሁል ጊዜ የአባቶቻችን ጀግንነት፣አንድነታቸውንና ጥንካሪያቸውን መዘከር ይጠበቅብናል በማለት ደስታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲያችን ለ127ኛ ጊዜ የተከበረው የአድዋ ድል በዓል 3(ሶስት) የጥናት ጽሁፎች በምሁራን ቀርቧል፡፡ እነኝህ ለውይይት የቀረቡት የታርክ፣የስነ-ጽሁፍና የስነ-ልቦና ተመራማሪዎች አቅርቧል፡፡ የታርክ ተመራማሪው ናትናኤል ለምለም ‹‹የአድዋ ድልና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሚና›› በሚል የመወያያ መነሻ ጽሁፍ አቅርቧል፡፡ ሁለተኛ የመነሻ ሀሳብ አቅራቢው የስነ-ጽሁፍ ተመራማሪ ዳንኤል መንግስቴ ‹‹አድዋ፣በአድዋ የተፈጠረች አርቲስት›› በሚል የእጅጋየሁ ሽባባው በአድዋ ድል የተቀናቀነችው የድል ዜማ ስንኝ በስንኝ አቅርቧል፡፡ ሶስተኛ የጽሁፍ አቅራቢው ረ/ፕ ዝናቤ ስዩም እና ዳርጌ የማነ ‹‹የአድዋ ድል የማሸነፍ ስነ-ልቦናዊ ጥበብ እና ቱሩፋቶቹ›› በሚል የአድዋ ድል የማሸነፍና ጥበብ የተሞላበት ድል መሆኑን አንስተው በቀረቡት ጽሁፎች ሰፊ ውይይቶችና ሀሳቦች ተነስተው በዓሉ በደማቅ ስነ-ስርዓት ፍጻሜ አግኝቷል፡፡       

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-

ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/

ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/

ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/

ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw


www.ddu.edu.et (https://www.ddu.edu.et/)

Dire Dawa | University

Dire Dawa University


www.ddu.edu.et (https://www.ddu.edu.et/)

Dire Dawa | University

Dire Dawa University


www.ddu.edu.et (https://www.ddu.edu.et/)

Dire Dawa | University

Dire Dawa University

Share This News

Comment