Logo
News Photo

የካቲት 25/2015 ዓ.ም “ብዝኃነት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል ለ2ተኛ ጊዜ የተዘጋጀውን ሀገር-አቀፍ የብዝሀነት ፎረም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

የብዝሃነት ፎረም ድሬዳዋ የምትታወቅበትንና ህዝቦቿ ተዋዶና ተፋቅሮ አብሮ መኖር የሚያጎላና በዘላቂነት በብዝሃትና አብሮ መኖር ላይ ምሁራዊ ውይይቶችና ጥናቶች የቀረቡበትና ምስራቁን የኢትዮጵያ ክፍል የሚወክል ፎረም በ2014 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ በፎረሙ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ህብረ-ብሄራዊነት መገላጫዋ፤ መደጋገፍና አብሮነት ተፈጥሮአዊ ስሪቷ፤ የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈርጥ፤ የትንሿ ኢትዮጵያ ገፀ-ውበት፤ የበረሀ ንግስት ወደ ሆነችው ድሬዳዋ እንኳን በሰላም መጣችሁ በማለት ጥሪያችን ተቀብለው ለመጡ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ተጋባዥ እንግዶች፣ጥናት አቅራቢ ምሁራን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡፡ ኢትዮጵያ የበርካታ ህዝቦች፣ ባህሎች፣ ሓይማኖቶች፣ ቋንቋዎች፣ ተፈጥሮ ሀብቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፤ ስርዓትና ወጎችን በጉያዋ ይዛ፣ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች፣ የሰው ዘር መገኛ የሆነች የዕድሜ ባለፀጋ ውብ ሀገር ናት ብለዋል፡፡ 

በፎረሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር አፌ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደም  በበኩላቸው  ድሬዳዋ የትንሿ ኢትዮጵያ ምሳሌና ጌጥ ሆና፤ የህዝቦችን አብሮነት በማድመቅ፤ ህብረ-ብሄራዊነት መለያ ውበቷ በመሆኑ ምክኒያት “የፍቅርና የመቻቻል ከተማ” ተብላ እንድትታወቅ ትልቅ ምክንያት ሆኗታል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ፈቲያ አያይዘው ብዘሃነት ለድሬዳዋ አዲስ አይደለም የአንድነታችን፣ ሉዓላዊነታችን፣ የጥንካሬያችንና የትልቅነታችን መገለጫ ማሳያና፤ ፈጣሪ የሰጠን ሀብታችን ነው በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡፡

የፎረሙ ቁልፍ መልዕክት አቅራቢው የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳየ ሲሆኑ ‹‹አካታች አገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ አስፈላጊነት›› በሚለ ሀሳብ ብዘሃነት የሰው ልጆች የባለ ብዙ ማንነት መገለጫቸው እና የፈጣሪ የእጅ ስራ ከከፍታና ዝቅታ ቦታዎች ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ አንስተው ለዚሁ ድሬዳዋ ትልቅ ተምሳሌ እንደሚትሆን በንግግራቸው አንስተዋል፡፡ 

በዚህ ፎረም ላይ ሁለት የጥናት ጽሁፍ ከፖለቲካል ሳይንስ ት/ት ክፍል በተመራማሪ ሱራፌል ጌታሁን  እና ከድሬዳዋ አስተዳደር የአስተዳደሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃላፊ በአቶ ሀብታሙ አሰፋ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ 

የዕለቱን መርሀ-ግብር  የዩኒቨርሲቲው ቢ/ል/ም/ፕ የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል ብዝሀነትን በተለያዩ ሁኔታ ማስጠበቅ እንደሚጠበቅ እና ለዚህም ማስፈፀሚያ መንገዶች መዘጋጀት እንዳለባቸው እንዲሁም ፎረሙ በቀጣይ በተለያዩ የብዝሀነት ሃሳቦች ለይ አጀንዳዎችን በማቅረብ የውይይት መድረኮችን ማመቻቸት አለበት በማለት የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-

ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/

ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/

ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/


www.ddu.edu.et (https://www.ddu.edu.et/)

Dire Dawa | University

Dire Dawa University

Share This News

Comment