Logo
News Photo

ምርምር ህትመትና ስርጭትን አስመልክቶ ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ስልጠና ተሰጠ

በዩኒቨርሲቲው የምርምር ህትመት፣ስነዳና ስርጭት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በምርምር ህትመትና ስርጭት (Research publication and Dissemination) ዙሪያ ከመጋቢት 1-2/2015 ዓ.ም.  የቆየ ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው መምህራን ተሰጠ። 

ስልጠናው ለተመራማሪዎች እና ለዩኒቨርሲቲው የሚኖረውን ፋይዳ በተመለከተ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ህትመት፣ ስነዳና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሙሐመድ ቃሶ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተርና  የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ወንድፍራው ደጀኔ በንግግራቸው ስልጠና የምርምር ውጤቶችን ተቀባይነት ባላቸው ተዋቂ ጆርናሎች ለማሳተምና የስርጭት ፕሮጄክት ለመቅረጽ ተመራማሪዎች ቀጣይ ለሚሰሯቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀው፤ ሰልጣኝ መምህራን ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ተጠቅመው የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ከአካባቢያቸው አልፈው ሃገርን ሊጠቅም የሚችል ስራ መስራት እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ስልጠና ስለሆነ መምህራን ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

በዚህ ለሁለት ቀናት በቆየው ስልጠና ላይ የምርምር ውጤቶችን በተለያየ መልክ ማሳተም፣ተዋቂና ተቀባይነት ያላቸውን ጆርናሎች መለየት፣ ኢምፓክት ፋክቶር፣ የምርምር ስነ-ምግባር፣ ፐላጃሪዝም፣ ፕረዲቶሪ ጆርናሎችን መለየት፣ የስርጭት ንድፈ-ሃሳብ ማዘጋጀትና በሌሎች ተያያዥነት ባላቸው ርዕሰ-ጉዳዩች ላይ ለመምህራን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ 

ስልጠናውን ከሐሮማያ ዩንቨርሲቲ በመጡት ተጋበዥ እንግዳ በፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ እንዲሁም ከዩንቨርሲቲያችን በዶ/ር አዲሱ ጌታቸውና ዶ/ር መሐመድ ቃሶ የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆኑ መምህራን ተሳታፊ እንደሆኑበት ለማወቅ ተችሏል።

Share This News

Comment