Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በልዩ ድጋፍ ኢንርንሺፕ ለሚወጡ ተማሪዎች የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ::

በ2015 ዓ.ም. ኢንተርንሺፕ ከሚወጡ ተማሪዎች መካከል ለተመረጡ 63 ተማሪዎች ከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች እንቅስቃሴ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በልዩ ድጋፍ የተሻለ የኢንተርንሺፕ ለሚወጡ ተማሪዎች የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር እሸቱ መኮንን እንደተናገሩት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይህ ፕሮግራም ከተጀመረባቸው ከሰባቱ አንዱ መሆኑን ገልጸው እድሉን የሰጡትን አካላት አመስግነዋል፡፡ አክለውም በዚህ ፕሮግራም ከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች እንቅስቃሴ ለ50 ተማሪዎች ለአራት ወራት በተከታታይ የሚደረግ የክፍያ ድጋፍ ለተመረጡ ተማሪዎች ያመቻቸ ሲሆን በትምህርት ክፍሎች መካከል ባለው የኢንተርንሺፕ ቆይታ ልዩነት ምክንያት በተደረገ ሽግሽግ እድሉ ለ63 ተማሪዎች እንዲዳረስ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑትም የቴክኖሎጂ ኢንስትቲትዩት፣ የጤና ሳይንስ እና የህግ ኮሌጅ ተማሪዎች መሆናቸው ገልፀው ተማሪዎች ያገኙት እድል በአግባቡ እንዲወጡ እና የፕሮጀክቱ ዓላማ ግቡን እንዲመታ ውጤት ተኮር ኢንተርንሺፕ ወቅት እንዲተጉ አሳስበዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው ስልጠና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኝ እና ከከፍታ ፕሮጀክት የቀረቡ የተለያዩ ርዕሶች ላይ ውይይት እና ገለፃ የተደረገ ሲሆን ከህግ ኮሌጅ 15፣ ከቴክኖሎጂ ኢንስትቲትዩት 20 እንዲሁም ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ 27 ተማሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Share This News

Comment