Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በጋራ በሚሰሩበት ዝርዝር ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሔደ፡፡

ድሬዳዋ የኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት በቅርቡ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው የሚታወስ ሲሆን ስምምነቱን  በፍጥነት ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል ምክክር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም ከድሬዳዋ ንግድ ቀጣና አመራሮች፣   የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተወካዮች እና ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን ወደ ትግበራ የሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል፡፡ በውይይቱም ላይ የስራ ቀደም ተከተሎች የተለዩ እና እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ድርሻውን የወሰደ ሲሆን በአጭር ግዜ በተቀመጠው የስራ ቅደም ተከተል መሰረት ወደ ትግበራ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

Share This News

Comment