Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲና የዳሽን ባንክ በቀጣይ በጋራ የሚያስራቸውን የመግበቢያ ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡

 ዳሽን በቅርቡ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ  በዩኒቨርሲቲው ለመክፈት ማቀዱንም አስታውቋል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን  የፈረሙት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ሲሆኑ  ፕሬዝዳንቷ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ከዳሽን ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት የተደረገው ስምነት ሁለቱንም ተቋማት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ በዳሽን ባንክ በኩል አቶ አየለ ተሾመ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር የመግባቢያ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡

በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ፣መምህራን እና ሠራተኞች በአቅራቢቸው አማራጭ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻሉም በዘለለ የተለያዩ የብድርና የፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ የጎላ ጥቅም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የዳሽን ባንክ ድሬደዋ ዲስትሪክት ስራ ስኪያጅ አቶ ጥላሁን ተንኮሉ በዚሁ ወቅት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ እንደገለፀት ባንኩ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማኅበረሰብ አገልግሎት ቀጣይ ተግባራት ለመፈፀም የጋራ የመግባቢያ ስምምነት መደረጉ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖራው አመልክተዋል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-

Share This News

Comment