Logo
News Photo

ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንገስት አገራዊ ዘመቻ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ፡፡

ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንገስት አገራዊ ዘመቻ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች /ፕሬዘዳንትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ / መገርሳ ቃሲም የነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ዘመቻን በዛሬው እለት መጀመሩን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አመልክተው በዚህ ዘመቻ ላይ ቁጥሩ 10,000 (አስር ) በላይ የሆኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተማሪዎች መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

"በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ላይ ያለአግባብ በአሜሪካ መንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን ጫና በመቃወም እውነታውን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆን ይገባዋል" ያሉት / መገርሳ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ሰላም በማስከበር ግዳጅ ላይ መስዋትነት እየከፈለ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊታችን 20 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ በመለገስ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

አሁን በአገር አቀፍ የተያዘው ዘመቻም እንዲሳካ ዩኒቨርሲቲው" ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት" ዘመቻን የተቀላቀለ ሲሆን መላው የዩነቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተማሪዎች ከመስከረም 13 - 14/2014 . ድረስ መምህራንና ተማሪዎች በትምህርት ክፍላችሁ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች በምታገለግሉበት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እና ሀገራዊ ግዴታችንን እንዲወጡ / መገርሳ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

"ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት" ዘመቻ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 15/2015 . የማጠቃለያ እንደሚከናወን ከወጣው ፕሮግራም ለማወቅ ተችሏል።

Share This News

Comment