Logo
News Photo

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕላንና ልማት ሚንስትር ሚኒስቴርና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በመገኘት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስጀመሩ::

2ኛው ምዕራፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእንድ ጀንብር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተካሄዷ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕላንና ልማት ሚንስትር ሚኒስቴርና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ 

በመርሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን ያኖሩ ሲሆን ችግኞቹን ተንከባክቦ በማሳደግም የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሠራተኞች የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ በችግኝ ተከላው ወቅት ጥሪ ተደርጓል፡፡ 

በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ 8 መቶ ሺህ ችግኞችን ለመትክል በእቅድ ተይዞ በዛሬው እለት በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ዞን ነፃ የንግድ ቀጠና ቅጥር ግቢ ውስጥ በተደረገው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሰላም ሚንስትር ሚኒስቴር የተከበሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የፕላንና ልማት ሚንስትር ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደምን የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራርሮችን ጨምሮ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በመጨረሻም በሀገር አቀፍ ደረጃ በእንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻን ማሳካት መቻሉ ታውቋል፡፡


Share This News

Comment