Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና በሠላም መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮ 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ አጠቃላይ ቁጥራቸው 14,780 (አስራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ)  የማኅበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ያለ ምንም ችግር በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንዳሳወቁት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተናውን እንዲወስዱ የተመደቡ የማኅበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተናው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ እና ስነ-ምግባርን ባከበረ መልኩ ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።
ዶ/ር ኡባህ አያይዘው ዩኒቨርሲቲው ከዝግጅት ምዕራፍ  ጀምሮ ያከናወናቸው ተግባራት ፈተናው ያለምንም ችግር በተያዘለት መርሃ-ግብር እንዲከናወን ያስቻለው መሆኑን አሳውቀው ፈተናው በመርሀግብሩ መሰረት ሰላማዊና በተሳካ መንግድ እንዲጠናቀቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካለት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Share This News

Comment