Logo
News Photo

በፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች ግምቱ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና መገልገያዎችን ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ድጋፍ አደረጉ፡፡

በፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች ግምቱ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ድጋፍ ያስረከቡ ሲሆን የቁሳቁስ ድጋፎቹም የህክምና መርጃ መሳሪያዎችን፣ አልጋ፣ ዊልቸር እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን የያዘ ድጋፍ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ በክቡር አቶ ከድር ጁሀር የተመራ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊችን ጨምሮ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ድጋፉን ያስረከቡት አቶ ሾኪ አሊ የተገኙበት የርክክብ መርሀ-ግብር ተካሄዷል፡፡
በድጋፉ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ክቡር ከድር ጁሀር ተገኘተው እንደገለጹት በራሳቸው ተነሳሽነት በፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆችን በማሰባሰብ እና በማስተባበር ለድጋፉ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉት አቶ ሾኪ አሊን አመድግነው ድጋፉ በዜጎች መካከል አብሮነትና የእርስ በርስ የመተሳሰብ ባህልን ለማጎልበት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ክቡር አቶ ከድር ጁሀር አያይዘው በውጭ የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች የድሬዳዋን ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት ለሚከናወኑ ስራዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የህክምና መገልገያዎችን ድጋፉን ያስረከቡት አቶ ሾኪ አሊ እንደገለጹት የድሬዳዋ ማህበራዊና የምጣኔ ሃብት ችግሮች በማቃለል ሂደት ላይ በፈረንሳይ የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች እንዲሁም ለአቶ ሾኪ አሊ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና በሆስፒታሉ ስም ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናውን ያቀረባል፡፡

Share This News

Comment