Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ Jhpiego HWIP ጋር በመተባበር ተቋማዊ የጥራት ግምገማ አውደ ጥናት አካሂዷል።

በአውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ የጤና ተቋም ኃላፊዎችና preseptors፣ Amref እና Jhpiego፣ የኮሌጅ ሰራተኞች እና የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል። ዶ/ር ሁሴን መሀመድ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር አድርገዋል። የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ Jhpiepo ፣HWIP እና Amref ለኮሌጅ ላደረጉት ተከታታይ ድጋፍ ዶ/ር ሁሴን  እውቅና ሰጥተወል፡፡ በኮሌጁ እስካሁን የተገኙትን አጠቃላይ ስኬቶችን ገልፀው ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ትኩረት ሰጥቷል። 

የጥራት ማጎልበት እና የአካዳሚክ ፕሮግራም ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ማሞ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በትምህርት ጥራት ላይ ማለትም በግብአት፣ ውጤት፣ አከሄድ እና ተፅዕኖዎች ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ሁሉንም ፕሮግራሞች በልዩ የህክምና እና የጤና ሳይንስ ፕሮግራሞችን እውቅና ለማሰጠት እየሰራ ነው። የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና የፕሮግራም ባለቤቶች ንቁ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ዶ/ር ዳንኤል አክለዋል። 

በአውደ ጥናቱ ላይ 3 ጽሑፎች የቀረበ ሲሆን ዶ/ር ሸጋዬ ይባቤ የህክምና ትምህርት ቤት ኃላፊ አጠቃላይ የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ ሂደቶችን ሀገራዊ እና በኮሌጅ ደረጃ የተሰሩትን በ3 መርሃ ግብሮች ማለትም በህክምና፣ በአንስቴዥያ እና በሚድዎይፈሪ እስካሁን የተገኙ ለውጦችን አቅርበዋል። 2ኛ ወረቀት በሚካኤል ኃይሉ የቀረበ ሲሆን በ Lincensure የፈተና አፈፃፀም እንቅፋት እና አመቻች ላይ የተካሄደ የድርጊት ጥናት በህክምና ና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ jhpiego HWIP ድጋፍ የተደረገ የተጠና ጥናት አቅርበዎል።

3ኛ ገለጻ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስርአተ ጾታ ጽ/ቤት አስተባባሪ ወ/ሮ ማወርዲ አደም የቀረበ ሲሆን በስርዓተ-ፆታ ፅ/ቤት አስተባባሪነት የተሰራውን እና ቢሮው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን አቅርበዋል።

ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በቀረቡት ፅሁፎች ላይ ፍሬያማ ውይይት ተደረጎ የማሻሻያ እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለትግበራ በጋራ አዘጋጅተዋል ። 

በመጨረሻም ዶ/ር ሁሴን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና የኮሌጅ ሰራተኞች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share This News

Comment