Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ STEM ማእከል ሲሰጥ የቆየው የ2015 ዓ ም ክረምት የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና የሂሳብ (STEM ) ፕሮግራም ስልጠና ተጠናቀቀ

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ከነሃሴ 1/2015 ዓ/ም ጀምሮ ከ7 - 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው ክረምት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና የሂሳብ (STEM ) ፕሮግራም ስልጠና ዛሬ ጳጉሜ 4/2015 ዓ/ም ተጠናቀቀ፡፡

በአሰተዳደሩ ከሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ካሉት ተማሪዎች መካከል የተሻለ ውጤት ያላቸው 200 (ሁለት መቶ) ተማሪዎች በክረምቱ መርሀ ግብር በሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ (STEM) ፕሮግራም ላይ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው ዕለት አጠናቀዋል፡

በስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አግልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በቆይታቸው በጽንሰ ሀሳብና በተግባር የታገዘ ትምህርት ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው ስልጠናው ተማሪዎቹ  በሳይንስ ትምህርቶች ተገቢውን ዕውቀት እና ክህሎት እንዲጨብጡ ከማድረግም ባሻገር ለፈጠራና ሳይንስ አዎንታዊ አመለካከት እንዲያዳብሩ የሚረዳ መሆኑን ጠቁመው ተማሪዎች በርትተው በማንበብ ነገ ቤተሰባቸውንና ሃገራቸውን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚያስጠሩ እንዲሆኑ በማለት የአደራ  መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ 

በተጨማሪም በዚህ ፕሮግራም ላይ በዩኒቨርሲቲው በ2015 የበጋው ፕሮግራም በቅዳሜና እሁድ ስልጠና ተከታትለው የተሻል ተሳትፎ የነበራቸው ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴርና Think young እና Addis coder በተሰኙ ተቋማት ትብብር በአዲስ አበባ በተዘጋጀ በሮቦቲክስ፤ አየር በረራ፤ ኮዲንግ ላይ ያተኮረ ልዩ ስልጠና የተከታተሉ ተማሪዎች ያገኙትን እውቀትና ልምድ ለተማሪዎቹ አካፍለዋል፡፡

በመጨረሻም በስልጠናው ለተሳትፉ ሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተቋጭቷል፡፡


Share This News

Comment