Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰብ ልጆች የሚውል የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ በየአምቱ በአስተዳደሩ ለሚገኙ አቅመ ድካማ ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በዚህም አመት የኑሮ አቅማቸው እጅግ ዝቅተኛ የሆኑና በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች የሚሆን ድጋፍ አድርጓል፡፡ 

ድጋፉን ለአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ያስረከቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በርክክቡ ወቅት አንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ባዛሬው እለት ያደረገው ድጋፍ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ  የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ነው ብለው ይህም ዩኒቨርስቲው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለአስተዳደሩ ከሚያደርጋቸው ዘርፈብዙ ድጋፎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የድሬደዋ ትምህርት ቢሮን በመወከል የትምህርት ቁሳቁሶቹን የተረከቡት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ ዩኒቨርሲቲው ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀው የአሁኑ ድጋፍ እንደ ሀገርና እንደ ድሬደዋ አስተዳዳር የተጀመረውን የትምህርት ጥራት ንቅናቄ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ 100 (አንድ መቶ) ደርዘን ደብተር እና 1000 (አንድ ሺህ) ስክሪፕቶ ድጋፍ ርክክብ ተደርጓል

Share This News

Comment