Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤት እድሳት አስጀመረ፡፡

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በድሬዳዋ አስተዳደር 133 የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት ለማድረግ እቅድ ተይዟል፡፡

አስተዳደሩ ከተለያዩ መንግስታዊ ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እና ድርጅቶች እንዲሁም ባላሀብቶችን በማስተባበር ነው እነዚህን የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት እያከናወነ የሚገኘው፡፡

ከእነዚህ 133 እድሳት ከሚደረግላቸው ቤቶች ውስጥ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የ5 ቤቶችን እድሳት የሚያደርግ ሲሆን በዛሬው እለትም የቤቶቹን እድሳት ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት በድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አስተዳደሩ የተለያዩ አካላትን በመስተባበር እያደረገ ባለው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአብዛኛዎቹ ቤት ግንባታና እድሳት በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

አስተዳደሩ የቤት እድሳት ብቻም ሳይሆን ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የቤት እቃዎችን የማሟት ሥራ በቀጣይ እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከተሰጡት የ5 የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት በዛሬው እለት ያስጀመረ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤቶቹን አጠናቆ ያስረክባል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎቱ ለአቅመ ደካማ ወገኖች በተለያየ መልኩ እገዛና ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው እነዚህም ድጋፍና እገዛዎች ከቀድሞ በበለጠ በአዲሱ 2016 ዓ.ም ተጠናክረው የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ካለፈው ሀምሌ ወር አንስቶ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በዚህም በርካታ ተግባራት መከናወናቸውም  በመርሀ ግብሩ ላይ ተገልጷል፡፡


Share This News

Comment