Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች አስመረቀ፡፡

በዩኒቨርሲቲው ላለፋት 2 ዓመታት ግንባታቸውን ሲከናወኑ የቆዩት ፕሮጀክቶች በድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ በተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ተመርቀው ተከፍተዋል፡፡ 

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅት በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል ሰለ ፕሮጀክቶች በዝርዝር ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን በዚህ መሠረትም  ሁለት የጥልቅ ውኃ ጉድጓድ ቁፋሮና ዝርጋታ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ መሆኑን እና የትራንስፎርመር ተከካው ተከላ ሲጠናቀቅ  ወደ አገልግሎት እንደሚገባ  ፣የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቤተ-መጽሐፍ ፣ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት መማሪያ ከፍሎች እና  7 የተማሪዎች የመኝታ ክፍሎች የመልሶ  ሙሉ እዳሳት እና ሶስት የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ ና አስር የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍሎችን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ (Smart class)  ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቀደም ብሎ ሙሉ ለሙሉ አገልግልት መስጠት አቁሞ የነበረን አንድ ህንፃ ሙሉ በማደስ ለአገልግልት ዝግጁ የማድረግ ሥራ መሠራቱን የጠቀሱት ዶ/ር ተማም የአንድ የኮሚኒቲ ፖሊስ አገልግልት መስጫ መዕከል ተገንብቶ ለአገልግልት ዝግጁ መደረጉንም በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅት አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹን መርቀው የከፈቱት በድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፕሮጀክቶቹ ዩኒቨርሲቲውን የጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ፊት የሚያስቀጥሉ ናቸው፡፡

በተለይ ዩኒቨርሲቲው ከራሱም አልፎ በቴክኖሎጂው አስተዳደሩን በብዙ መልኩ መጥቀም የሚችልብትና አብሮ ተጋግዞ ተናቦ መጓዝ የሚያስችለውን አቅም የሚፈጠር ነው ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳነት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ ለአገልግልት መብቃቱ ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲው ከንፁ መጠጥ ውሃ ጋር ተያይዘው ይነሱ የነበሩ ችግሮችን ከመቅረፉ ባሻገር በቅጥር ግቢያችን ውስጥ የጀመርነውን የአረንጓዴ አሻራን መርሀግብር የሚፈለገው ደረጃ ላይ መድረስ እንድንችል ትልቅ እገዛ ይኖረዋል፡፡

ሙሉ እድሳት በማድረግ በቴክኖሎጂ የዘመናቸው የድህረ-ምረቃ የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎቻችን ደግሞ ከዚህ ቀደም በእንግድነት የተለያዩ ኮርሶችን ለሚሰጡ መምህራን ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ የቀነሰና ከመቀነሱም በላይ ዩኒቨርሲቲው በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በቅርብ ባቋቋማቸው ሳተላይት ካንፓሶች ትምህርት በኦላይን መስጠት የሚያስችለው በመሆኑ ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡- 

Share This News

Comment