Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2015 በጀት ዓመት በሥራቸው የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ መምህራን ፣ሠራተኞች፣ አጋር እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እውቅና ሰጠ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የተከበሩ ም/ከንቲብ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ የድሬደዋ ፖሊስ  ጠቅላይ መምሪያ ኮምሽን ኮምሽነር አለሙ መገራ የሀይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2015 በጀት ዓመት ከእቅድ ከንውኑ አንፃር ባመጣው የተሻለ ውጤት  የላቀ አስተዋፅኦ አበርክተዋል በማለት በስነ-ስርዓቱ እውቅና የሰጣቸው በግለሰብ ፣ በኮሌጅ ፣በትምህርት ክፍል ደረጃ እና ከውጪ አጋር አና ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ናቸው፡፡

በዚህ መሠረትም የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በስነ-ስርዓቱ ላይ በልዩ ተሸላሚነት እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ፕሮጅክትን በብቃት በመምራት፣ ፈንድ በማፈላልግና በማምጣት፤ ፕሮጀክቱን በወቅቱ በማጠናቀቅ እና የሚሰሩትን ምርምር በጊዜ በማጠናቀቅ ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ የአውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ቴክኖሎጂን ለማህበረሰብ በማስተላለፍ /ትራንስፈር/ በማድረግ የህብረተሰቡን ችግር በመፍታት የነ ዶ/ር ግርማ ቤካ ቡድን ፣በሶፍትዌር በማበልፀግ የቅጅ መብት ያስገኙ መምህር ዳመና ደስታ ፣  አንድነት አሰፋ ፣  ዶ/ር ጋዲሳ ኦላኒ እና   መ/ር ጌትነት ቶሎሳ እንዲሁም መ/ር መርክነህ አብረሃም የዩኒቨርሲቲውን የጤና ቡድን ለተከታታይ 3 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በማሰልጠን በግልና በቡድን የእውቅና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና  ብዙ ተማሪ ባሳለፈ፣ የምርምር ግራንት/ፈንድ/ በማስገኘት ፣ የሲቪል ምህንድስና እና አርክቴክቸር ት/ቤት ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እና የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እውቀቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንዲሁም የሜካኒካል እና ኢንዱስትሪያል ት/ት ቤት  የተለያዩ የመገልገያ ቁሳቁሶችን በመሥራት ዩኒቨርሲቲውን ከተለያዩ ተጨማሪ ወጪ በማዳን ዩኒቨርሲቲው በራሱ አቅም ችግሮቹን እንዲፈታ በማስቻሉ የእውቅና ከተሰጣቸው ኮሌጆች መካከል የተካተተ ነው፡፡

በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲው ለውጪ ባለድርሻ አካላት እውቅና የሰጠ ሲሆን በዚህ መሠረትም በመውጫ ፈተና ወቅት፣ የ12 ክፍል ፈተና እነዲሁም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማር አእንዲሳካ ላደረጉ በድሬዳዋ አስተዳደር የሃማኖት ተቋማት ጉባዔ፣  ኢትዮ-ቴሌኮም ድሬዳዋ ዲስትሪክት ፣ የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣ ፌዴራል ፖሊስ፤  የድሬደዋ ከንቲባ ጽ/ቤት ፣ የድሬደዋ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ድሬዳዋ ፖሊስ ኮምሽን፡፡  እንዲሁም ለመምህራን እና ተማሪዎች የተግባር ተኮር ትምህርት በመስጠት ድጋፍ ላደረጉ  ለኒው ዌቭ ኃ.የ.ካ ፣ለሀና ፕላስት መኑፋክቸሪንግ  ኃ.የ.ካ ፣ ዉሺ ነበር ዋን ጨርቃ ጨርቅ ኃ.የ.ካ ፣ አሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴስ ፣ SOS ህፃናት ማሳደጊያ መንድር  ፣ኢትዮ ኢታሊ -ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ድሬደዋ ጤና ቢሮ ፣ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ሸሙ ኃ.የ.ካ ፣ ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ ካንፓኒ ፣ኮኔል ፋክተሪ ፣ናሽናል ሲሚንት ፣ኦክስፋም ግሬት ብሪትን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፣ለሰዎች ለሰዎች አግሮ ቴክኒካል ኮሌጅ ፣ለድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ፣ለኢንደስተሪ ፓርኮች ኮርፕሬሽን ድ.ዳ ቅርንጫፍ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡- 

Share This News

Comment