Logo
News Photo

የአለም አቀፉ የአዕምሮ ጤና ቀን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ

የዘንድሮው የአለም አቀፉ የአዕምሮ ጤና ቀን ”የአዕምሮ ጤና ለሁለንተናዊ የሰው ልጆች መብት ” በሚል መሪቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

ይህንኑ በማስመልክት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ከዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የፓናል ውይይት አዘጋጅቷል፡፡


በዚሁ የፓናል ውይይት መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ የአዕምሮ ጤና በአሁኑ ሰዓት በአገራችንም ሆነ በአስተዳደራችን ድሬዳዋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡ በዚሁ ሳቢያ ለከፋ የጤና ችግር ሚጋለጡ ወገኖች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ሁሉም አካል ለጉዳዩ ከቀድሞ በበለጠ ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ዶ/ር ወንዲፍራው አስገንዝበዋል፡፡


በዚሁ የፓናል ውይይት ላይ በሳይኮሎጂ የትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቤ ስዩም እና የህግ ኮሌጅ  መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር እነዳወቅ ፀጋው ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የአዕምሮ ጤና ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ መከበር እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

Share This News

Comment