Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከቢፍቱ በሃ ኦሮሚያ የንግድ አክስዮን ማህበር ጋር የሁለትዮሽ የስራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ዩኒቨርስቲው በድሬዳዋ አስተዳደር እየተስፋፉ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ና ተቋማት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በየዘርፉ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በተለይ ዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ ብቃትና ጥራት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማፍራት ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የቢፍቱ በሃ ኦሮሚያ የንግድ አክስዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሲን መሐመድ በበኩላቸው ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈጠረው ትስስር ማህበሩ በተሰማራበት የግብርና ምርቶች ወደ ውጭ አገራት የመላክ የንግድ ስራ ዘርፍ ተወዳዳሪ ና አሸናፊ ለመሆን ያስችለዋል ብለዋል።

በተለይ ማህበሩ በቀጣይ የአበባ፤ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ወደ መካከለኛ ምስራቅ አገሮች ደረጃቸውን ጠብቆ በጥራት ለመላክ የጀመረውን ስራ ስኬታማ እንዲሆን መሠረታዊ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አቶ ያሲን ተናግረዋል ።

70 ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ቢፍቱ በሃ ኦሮሚያ አክስዮን የንግድ ማህበር ባለፉት ሁለት አመታት ከጫት ንግድ ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱ የተገለፀ ሲሆን አሁን ግን ከጫት ንግዱ በመውጣት በሌሎች የግብርና ምርቶችና በአበባ ስራ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

Share This News

Comment