Logo
News Photo

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን የተመለከተና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በትብብር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት ተጀመረ፡፡

በቢ-ካፒታል ሆቴል በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የባለድርሻ አካላቶች የፓናል ውይይት በዋነኝነት የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፕሬሽን ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፣giz እናUK AID ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር እንዳሉት ድሬዳዋ የምስራቁ አፍሪካ ቀንድ የንግድና የኢንደስትሪ መዕከል የመሆን ርዕይዋን ማሳካት እድትችል ነፃ የንግድ ቀጠናው መቋቋሙ መንገድ ከፋች ነው ብለዋል ፡፡ ለዚህም አስተዳደሩ የበኩሉን ሁሉ ድገፋና እገዛ ያደርጋል ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሠ በበኩላቸው የድሬዳዋ የነፃ የንግድ ቀጠና 2.2ቢሊየን ብር የሚገመት ገቢ  እስካሁን ባለው በኤክስፖርትና በተተኪ ምርት ማስገኘት ችሏል፡፡ 

ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን ጠቁመው ነፃ የንግድ ቀጠናው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ የድሬዳዋንም ሆነ የአገር ልማትን ከማፋጠን አንፃር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ የነፃ የንግድ ቀጠና ምንነት ፣ጠቀሜታውን ፣ተግዳሮቶቹን እና የባለድርሻ አካልት ሚናን በተመለከተ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዶ/ር አማረ ማህተቡ ነፃ የንግድ ቀጠናን በተመለከተ የአለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እንዲሁም አቶ ኤርሚያስ መለሰ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን የነፃ የንግድ ቀጠናን በተመለከተ ህጎችና አዋጆችን አያይዘው ፅሁፋቸውን አቅርበዋል፡፡   

ከዚህ በተጨማሪ በውይይት መድረኩ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በፓናሊስትነት የተገኙ ሲሆን ለቀረቡላቸው  የተለያዩ ጥያቄዎችም ገለፃና ማብራሪያ በማከል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በድሬዳዋ ቢ-ካፒታል ሆቴል የተጀመረውና ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቀጥለው የፓናል ውይይት በዛሬው እለት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ከነበረው መድረክ በተጨማሪ ነገ ከባለሀብቶችና የፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም አርብ ከተማሪዎች ጋር የውይይት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ችለናል፡፡

Share This News

Comment