Logo
News Photo

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን አስመልክቶ ሲደረግ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ የፓናል ውይይት ተጠናቀቀ፡፡

ባለፈው እሮብ በድሬዳዋ ቢ-ካፒታል ሆቴል የተጀመረው የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲካሄድ የነበረው  የፓናል ውይይት ዛሬም በሦስተኛ ቀን ውሎው ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከሎሎች ዩኒቨርሲቲና የፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የተውጣጡ ተማሪዎች እና መምህራን ጋር ውይይት በማካሄድ ተጠናቋል፡፡

በፓናል ውይይቱ የድሬደዋና የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሁም የድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክና የኢትዮ- ጣሊያን ፖሊ-ቴክኒክ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

የፓናል ውይይቱን እንኳን ደህና መጣቹህ በማለት በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መቋቋሙ ከአካባቢው አልፎ ለአገር እድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች እንዳሉት ገልጸው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀጣናው ዋና አጋር መሆኑን አስታውሰዋል ፡፡ አክለውም ነፃ የንግድ ቀጠናው ዩኒቨርሲቲው ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማሳካት የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ የሚያገኙበት ዩኒቨርሲቲው ደግሞ የሰለጠነ የሰው ኃይልን በማፍራትና በጥናትና ምርምር የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ የሚሄድብትን ሰፊ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ ይሄን የተፈጠረ እድል ደግም ተማሪዎች ተጠቅመው በቀጣይ ራሳቸውን በክህሎት በማብቃት ተፎካካከሪና በሥራቸው ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንደስትሪ ትራንስፎርሜሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ መሰለ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩ በአገራችን እስካሁን 13 የኢንደስትሪ ፓርኮችን ማቋቋም የተቻለ ሲሆን በእነዚህም ከ100 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጅምሮች በማስፋትና በተለይ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የሚደረገው ጥርት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ለአንድ ቀን በሚቆየውና በዋነኝነት የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፕሬሽን፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፣UK AID ,German cooperation ,giz እና Sustainable Industrial Clusters ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የፓናል ውይይት ላይ የተለያዩ ነፃ የንግድ ቀጠናን በተመለከተ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ነፃ የንግድ ቀጣናውን በመጎብኘት ተጠናቋል፡፡

Share This News

Comment