Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር በመጡ የክትትልና ድጋፍ ልዑካን ቡድን ሲደረግ የነበረው የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ ተጠናቀቀ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር  የክትትልና ድጋፍ ልዑካን ቡድን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመስክ ምልከታ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ቀን ውሎ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በዚህ ወቅትም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት በዩኒቨርሲቲው በእቅድ ተይዘው የተከናወኑ ተግባራትን ለልዑካን ቡድኑ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በማስቀጠልም የልዑካን ቡድኑ አባላት ከመምህራንና ከተማሪዎች ከተውጣጡ እና ከዩኒቨርሲቲውርካውንስል አባላት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

የክትትልና ድጋፍ ልዑኳን ቡድኑ አባላት በመስክ ምልከታቸው በዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ የተማሪዎች አገልግልት እና በመገንባት ላይ ያሉና የተጠናቀቁ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር የክትትልና ድጋፍ ልዑኳን ቡድኑ በሦስት ቀን ቆይታቸው የነበረውን አጠቃላይ ሪፖርት ለዩኒቨርሲቲው በግብረ መልስ መልክ በትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ልማት ዘርፍ ዴስ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዶ ናስር ያቀረቡ ሲሆን በዚህ መሠረትም የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተለይ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኢ-ለርኒንግ የመማር መስተማር ስርዕትን ለመዘርጋት የአይ.ሲ.ቲ የዳታ ሴንተር የመሠረተ ልማት ሥራ እጅግ የሚበረታታና ለሌሎችም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደ አርያ የሚወስድ መሆኑን ገልጸው  ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲነሳበት የነበረውን የንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦ ችግር ጥያቄን መፍታት የቻለበት ሂደት የልዑኳን ቡድኑ አድንቆ ከመፀዳጃ ቤት ጋር ተያይዞ የሚነሱት ችግሮን ለመፍታት እየተሠሩ ያሉ የእድሳትና የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት አለባቸው ብለዋል፡፡

በዩንቨርስቲው የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ተጠናክረው በማስቀጠል መፈታት ያለባቸውን የመማር ማስተማር ግብአቶችና የትራንስፖርት አቅርቦት ችግሮች መፍትሔ እንዲሠጣቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በመጨረሻም በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ተጠናቀው በቅርቡ አገልግሎት ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኙት የተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈፃፀማቸው ጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ እና በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም  በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ እንዲወጣ እየሰራቸው ያሉትን እንቅስቃሴዎችን የልዑኳን ቡድኑ በአካል በመገኘት መመልከቱን አድንቀው መፍትሔ የሚሹ ችግሮችን ዪኒቨርሲቲው ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

Share This News

Comment