Huawei Ethiopia ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል Huawei ICT Competition ላይ ገለፃ አደረገ፡፡
ህዋዊ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ መሠረቱን በቻይና ሀገር ያደረገ ግዙፍ ድርጅት ሲሆን ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በHuawei ICT Academy እና በተለያዩ መስኮች ተቀራርቦ እየሠራ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚን በመክፈት ለተማሪዎች እና ለአካባቢ ማህበረሰብ በHuawei Technology የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠትና ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ከመማር ጎን ለጎን የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው እየሰራ እንደሚገኝ በድርጅቱ የኢኮ ሲስተም ማናጀር የሆኑት አቶ እንዳለ ረጋሳ ተናግረዋል፡፡
ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ፣ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ለሶፍተዌር ኢንጅነሪንግ እና ለኮንፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የHuawei ICT አስመልክቶ ለግማሽ ቀን በቆየ ፕሮግራም ላይ በመገኘት አቶ እንዳለ ማብራርያ ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ የተደረገው ገለፃና ማብራሪያ በተለይ ተማሪዎች ህዋዊ ኢትዮጵያ በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የእርስ በእርስ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሆነው የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቻይና ሀገር በመሄድ ተጨማሪ ስልጠና እና ትምህርት ማግኘት የሚችሉብትን እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ስንታየሁ አለሙ በበኩላቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዙርያ ተማሪዎች ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ Huawei ICT Academy፣ Cisco Academy፣ Oracle Academy ጨምሮ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን መስጠት የሚያስችል የአይሲቲ አካዳሚ የአጠቃቀም መመሪያ በዩንቨርስቲው ማኔጅመንት በማጸደቅ ስልጠናዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸው ማንኛውም ፍላጎት ያለው በአይሲቲ አካዳሚው የሚሰጡትን ስልጠናዎች ምዝገባ በማከናወን መውሰድ እንደሚችሉ አሳውቀዋል።
Share This News