Logo
News Photo

በአካዳሚ ጉደዮች ም/ፕሬዚዳንት የተመራው የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ካዉንስል በዩኒቨርስቲው እየተሰራ ያለዉን የመሰረተ ልማት ስራዎችን ጎበኙ።

በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚ ጉደዮች ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እና የቀድሞ ቢዝነስና ልማት ም/ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ተማም አወል የተመራ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ካዉንስል ቡድን ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ያሉትን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸውም በተወዳጁ አርቲስት አሊ ቢራ የተሰየመው ዘመናዊ ቤተ- መጽሐፍት፣ የተማሪዎች ከፍተኛ ክልኒክ፣ እየተገነባ ያለው የመምህራን መኖሪያ በተጨማሪም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራልና ማስተማሪያ ሆስፒታል ተጎብኝቷል።


የአካዳሚክ ካዉንስል ቡድኑ ጉብኝት አላማ በዩኒቨርስቲው እየተሰራ ያለው የተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ለአመራሮቹ ግንዛቤ እንድያገኙ ማድርግ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።


Share This News

Comment