Logo
News Photo

በድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የ10 ዓመት የኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈረመ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር የተፈራረመው  የሁለትዮሽ ሰምምነት በድሬዳዋ የጥቃቅንና መካከለኛው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለ10 ዓመት  የሚመራበትን የኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ነዉ።

የሁለትዮሽ ስምምነት ሰነዱ ላይ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የቢሮዉ ኃላፊ የሆኑት ክቡር ሀርቢ ቡህ ሲፈርሙ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በኩል ደግሞ የዩኒቨርስቲዉ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል ፈርመዋል፡፡

በስምምነት መድረኩ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅምን ለማሳደግና በተተኪ ምርቶች ላይ የግብአት እጥረትን ለመቅረፍ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ተገልፃል።

የኢንዱስትሪና ዩኒቨርስቲ ቀጠናዊ ትስስር ውጤታማ እንዲሆን የአስተዳደሩን አምራች ኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ በመቅረፅ ኢንዱስትሪ የማማከር አገልግሎት የቢዝነስና ቴክኒካል ክህሎት ስልጠና መምህራን በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የተግባር ልምምድ በማድረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፎችን እንደሚሰጥም በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለዉን ቅንጅታዊ አሰራርን ለመፍጠር  የስምምነት ሰነድ መፈረሙ ድሬዳዋ የምስራቁ ክፍል የኢንዱስትሪ ኮሪደር ለመሆን የያዘችዉን ርዕይ ለማሳካት ትልቅ እገዛ እንደሚኖረዉ በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Share This News

Comment