Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለአብዲ ቦሩ የእግር ኳስ ፕሮጀክት ግምቱ 200 ሺህ ብር የሚጠጋ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ድጋፉን ለስፖርት ፕሮጀክት ኃላፊው ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ለስፖርት ቡድኑ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረው ዛሬ የተደረገው የትጥቅ ድጋፍም ዩኒቨርሲቲው ቡድኑን በዘለቂነት ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ 


የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ለአብዲ ቦሩ የእግር ኳስ ፕሮጀክት ከስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ድጋፍ ባሻገር በዩኒቨርሲቲው የስፖረት ሳይንስ ት/ት ክፍል መምህራንን አማካኝነት ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ድጋፍ በቀጣይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው በዛሬው እለትም የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ የአካባቢውን ወጣቶችና ታዳጊዎች ነገ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ ዩኒቨርሲቲው ለአብዲ ቦሩ የታዳጊና ወጣት የእግር ኳስ ፕሮጀክት በድጋፍ መልክ ያበረከተው የስፖርት ትጥቅ ከ200 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ገልጸው ድጋፍ የተደረገላቸው የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የስፖርት ትጥቆቹን በአግባቡ በመጠቀም ለውጤታማነት እንዲሰሩና የዩኒቨርሲቲውን ብሎም ድሬዳዋን ስም እንዲያስጠሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share This News

Comment