Logo
News Photo

አለም አቀፉ የፀረ-ሙስና ቀን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

”ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው ፤ በህብረት እንታገለው” በሚል መሪ ቃል በአለምና በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ-ሙስና ቀንን አስመልክቶ ለግሽ ቀን የቆየ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጅቷል፡፡


በፓናል ውይይቱ መክፈቻ ላይ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ባስተላለፉት መልዕክት ሙሰና አገራችን የጀመረችውን ፈጣን የልማት ጉዞ በማደናቀፍ ረገድ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ በጋራ ልንከላከለው ይገባል፡፡

ሙስናና ብልሹ አሠራር እንደተቋም ባለን ውስን ሀበት የሚያስከትለውን ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በመከላከሉ ረገድ በጋራ በመሆን ሊረባረብ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።


በፓናል ውይይቱ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሄኖክ አየለ አዘጋጅነት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ በፓናል ተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡


በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የመካከለኛ አመራር ደረጃ ላይ የሚገኙ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎች የሃብት ምዝገባ አከናውነዋል፡፡

Share This News

Comment