Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንንና የአስተዳደር ሠራተኞ ሃገር ያቀረበችውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር መዝመትን ጨምሮ ደገፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው ተገለፀ።

ወቅታዊ አገራዊ ጉዳን አስመልክተው በጋራ የተሰባሰቡት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን የአሸባሪን ቡድን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ የክቡር ጠቅላ ሚኒስትራችን ጥሪ ተቀብለን ወደ ግንባር እንዘምታለን ሲሉ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞቹ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስተራችን ጦር ግንባር ሆነው እኛ ቤት ቁጭ አንልም ያሉት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ሀገራችን በምትፈልገን በሁሉም መስክ ለመሰለፍ መዘጋጀታቸውን የገለፁ ሲሆን በተለይም በአሁኑ ሰዓት ሀገርን ለማዳን ለሚደረገው ርብርብ በቀዳሚነት በመሰለፍ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋትንት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል ፡፡
ይህንኑ መድረከ የመሩት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለጹት በአሁኑ ሰዓት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለመናድ ከምንግዜውም በላይ ከውስጥም ከውጪም ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑን ሆላችንም አውቀን ሀገርን በማዳኑ ዘመቻ ላይ ሁላችንም በምንችለው አቅም ተሳታፊ መሆን ግድ ይለናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ኡባህ አክለውም መላው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሠራዊታችን የአንድ ወር ደሞዙንና የደም ልገሳ እንዲሁም ከሰሜን ወሎ አካባቢ ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ 1.5 ሚሊዮን (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን በማንሳት በአሁኑ ሰዓትም ለመከላከያ ሠራዊታችንና ለተፈናቀሉ ወገኞቻችን የሚደረገው ድጋፍ አጠናክረን ከመቀጠል ባለፈ ግንባር ድረስ በመዝመት ሃገርን ለማዳን ዝግጁ እንዲሆኑ አስገንዝበዋል።

Share This News

Comment