Logo
News Photo

በኢትዮጽያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት የሚያስችል የዲጅታል ትምህርት መስጫው የኢ-ለርኒንግ መልቲሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ሥራ እየተፋጠነ መሆኑን ተገልፆል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን /Mastercard Foundation፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ /Arizona State University 50ዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) ጋር በመሆን እየተገበረ ያለው ኢ-ለርኒንግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት (e-Learning for Strengthening Higher Education / e-SHE) የተሰኘው የአምስት ዓመት ፕሮጀክት በኢትዮጽያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ ውጥኖችም 

1. ሀገር አቀፍ የኢ-ለርኒንግ ፖሊሲ ማዘጋጀት፣ 

2. በ5 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርት የሚዘጋጅባቸው ደረጃቸውን የጠበቁ መልቲ ሚድያ ስቱዲዮችን መገንባት፣ 

3. ለመምህራንና ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን መስጠት፣ 

4. የዲጂታል ትምህርት ሥርዓትን መዘርጋትና ሁለት ሞዴል የዲጂታል ኮርሶችን ማዘጋጀት ይገኙበታል፡፡

በዚህም የትምህርት ጥራት፣ ተደራሽነትንና አግባብነትን ለማረጋገጥ መሰረት ይጥላል፡፡ 

ፕሮጀክቱ በተለይም በዲጂታል ትምህርት ዘርፍ ያለውን የፖሊሲ ክፍተት ለመሙላት የኢ-ለርኒንግ ትምህርት ፖሊሲንና መመሪያን ለማርቀቅ ሲያከናውነው የነበረው ሥራም ተጠናቆ ፖሊሲው በትምህርት ሚኒስቴር መጽደቅ ችሏል።


ፕሮጀክቱ 50 የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመድረስ የወጠነ ሲሆን በተለይም በCluster Resource Center ተብለው በተለዩ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የዲጂታል ትምህርት የሚዘጋጅባቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የመልቲ ሚድያ ስቱዲዮዎችን እየገነባ ይገኛል።


በአቅም ግንባታ/Capacity Building የትኩረት አቅጣጫው የመምህራንና የተማሪዎችን የዲጂታል ትምህርትን የመስጠትና የመከታተል አቅምን የመገንባት እቅድን ይዟል። የፕሮጀክቱ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ 35,000 መምህራን እና 800,000 ተማሪዎችን ለመድረስ ታቅዷል።

ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመምህራን የዲጂታል ትምህርት አዘገጃጀትና አሰጣጥን የተመለከተ ስልጠና በመሰጠት ላይ ሲሆን ለተማሪዎች የዲጂታል ትምህርትን እንዴት መከታተል እንደሚችሉና የበይነ መረብ ደህንነትን የተመለከቱ ሥልጠናዎች/ኮርሶች ተዘጋጅተዋል። 


በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርት እንዲሰጡ የሚያስችላቸውን የLearning Management System (LMS) እና Student Information System (SIS) በመዘርጋት ላይ ነው።

ከዚህ ባለፈ በተመረጡ የትምህርት ባለሙያዎችና መምህራን በመታገዝ የዲጂታል ትምህርት ማስጀመሪያ የሚሆኑ ሁለት ሞዴል Emerging Technologies እና Mathematics for Natural Science ኮርሶች ዝግጀት የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህ የትምህርት ዓመት የገፅ ለገፅ ትምህርትን እንደ ማጣቀሻ ሆነው እንዲያግዙ የሚደረግ ይሆናል። 


ከእነዚህ የኢ-ለርኒንግ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ እነዲገነቡ ከታሰበባቸው 5 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው በመገንባት ላይ ያለው የኢ-ለርኒንግ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ የግንባታ ሂደት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እና ከShayashone PLC ጋር በመሆን የግንባታውን ጎብኝተዋል፡፡


Share This News

Comment