Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ የማስተማሪያ ዘዴዎችና የሞያ ማሻሻያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ለአንድ ቀን የቆየውን ስልጠና ያዘጋጁት የኢትዮጵያ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ማህበር፤ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከብርቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር ነው፡፡

ይህንኑ የስልጠና መድረክ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በንግግር የከፈቱ ሲሆን የዚህ አይነት ፕሮግራሞች በሃገራችን ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትና ሥልጠና ጋር ተያይዞ በተማሪዎች ላይ የሚታየውን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡ 


በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል (ELIC) አስተባባሪ አቶ ነቢል መሃመድ በበኩላቸው የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህራን በሞያ ማሻሻያ ስልጠናዎች ማገዝ የሚታየውን ችግር መፍታት እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡ 


በእለቱ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ ላይ የረጅም ጊዜ የማሰልጠን ልምድና እውቀት ያላቸው ምሁራን ለተሳታፊዎች በተግባር የታገዘ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በዋንኝነትም Project-Based Learning English Language Fellow, Managing Resources, Climate in ELT, Fillers, Warmers & Coolers እና English Connects በተሰኙ በ5 ርዕሶች ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment