Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሳምንት ተከበረ፡፡

በየዓመቱ የሳይንስ ሳምንት በሀገር-አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን ይህንን በዓል በማስመልከት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል አዘጋጅነት የሳይንስ ሳምንት ተከብሯል።

በፕሮግራሙ ላይ በሳ.ቴ.ም.ሂ ማዕከል (STEM Center) በ2015 ዓ.ም በበጋው መርሀ-ግብር ሲማሩ የነበሩና የተሻለ ፕሮጀክት በመስራት በ2016 የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ሀገር-አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና ውድድር ላይ የተካፈሉ ተማሪዎች የሰሯቸውን ፕሮጀክቶች ለታዳሚው አቅርበዋል።

ፕሮግራሙ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጋበዙ ተማሪዎች፣ መምህራን ና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መካፈላቸው ታውቋል።

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲውን በመወከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በነበረው ውድድር ላይ ለተሳተፉት ተማሪዎች፤ ተማሪዎቹ ለሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶችና፤ ተማሪዎቹን ለውጤት ላበቃው መምህር የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። 

Share This News

Comment