Logo
News Photo

የ18ኛው ብሔር ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ሲከበር መድረኩን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በንግግር ከፍተዋል፡፡


ዶ/ር መገርሳ በንግግራቸው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የብሔሮቹ የቃል ኪዳን ሰነድ የሆነው ህገ መንግስት የጸደቀበትን ታሳቢ ተደርጎ የሚከበር መሆኑን አንስተዋል።


ቀኑ ለተከታታይ ዓመታት በመከበሩ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያስገኛቸው በርካታ ትሩፋቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።


በቀጣይም እኩልነት የተረጋገጠባትና ፍትሀዊነት የነገሰባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የምናደርገው ጥረት ከዳር ይደርስ ዘንድ ሁላችንም ለአገራችን በምንችለው ሁሉ አስተዋፅኦዋችንን በተጠናከረ መልኩ ማበርከት ይኖርብናል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


በመድረኩ ላይ በዩኒቨርሲቲው የህግ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ረ/ፐረ እንዳወቅ ፀጋው ”ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራል ስርዓት እና የሰላም ግንባታ” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በተሳታፊዎች በኩል ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Share This News

Comment