Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና በድሬዳዋ ኢትዮ ጣልያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በስልጠና፣ በማማከር፣ በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት በጋራ ለመስራት ዓላማ ያደረገ የመግባቢያ ሰነድ በሁለቱ ተቋማት መካከል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተፈርሟል፡፡ 


በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል ፊርማቸውን ያኖሩት የምርም እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል እንደተናገሩት ሁለቱ ተቋማት በተናጠል የሚያደርጉት ጥረቶች ውጤቶችን በሚፈለገው መጠን የሚያመጣ ባለመሆኑ የመግባቢያ ሰነዱ ተቋማቱ  በእሴት ሰንሰለት ውስጥ  ያለውን የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ተቀራርበው እንዲሰሩ መሰረትን እንደሚጥል እና በቀጣይነት ትስስሩን በማሳደግ በርካታ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ ጥምረቶችን ለመመስረት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል፡፡ 


ትስስሩን በተግባር ለማስጀመር በቀጣይ ከሁለቱም ተቋማት የሚዋቀር የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ በመግባቢያ ሰነዱ  መሰረት ስራዎች በተቀመጠላቸው ጊዜ እና በሚፈለገው ደረጃ እንዲተገበሩ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡


Share This News

Comment