Logo
News Photo

በክረምት የበጎፈቃድ ጤና አገልግልት አስተዋፅኦ ለነበራቸው እውቅና ተሰጠ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም እንደ ድሬዳዋ አስተዳደደር በክረምት በጎፈቃድ የጤና አገልግልት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በክረምት በጎፈቃድ የጤና አገልግልት ባከናወናቸው ተግባራት በኢትዮጵያ ከሚገኙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል የተሻለ አፈፃፀም በማምጣት ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡


በዛሬው እለትም ለዚህ ስኬት መገኘት  የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው  ዩኒቨርሲቲው  እውቅና የሰጠ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ በመገኘትም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በክረምት የተጀመሩት የበጎፈቃድ ተግባራት በበጋም ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


በዚሁ የእውቅና ፕሮግራም ላይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሰቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሎጅ ዲን ዶ/ር ሁሴን መሀመድ በዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም በክረምት የበጎፈቃድ ጤና አገልግልት የተሠሩ ሥራዎችን በቅደም ተከተል አቅርበው በዝርዝር ለተሳታፉዎች አቅርበዋል፡፡


በመጨረሻም በክረምት በጎፈቃድ የላቀ አስተዋጽዖ ለነበራቸውና ለሥራው መሳካት እገዛ ለነበራቸው አጋር አካላት የእውቅና የምስክር ወረቀት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እጅ ተረክበዋል፡፡

Share This News

Comment