Logo
News Photo

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራን የኢንተርፕረነርሺፕ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጀመረ፡፡

በኢንዱስትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት /EDI/ ጋር በመተባበር ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና /ToT/ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ተማም አወል EDI ላደረገው ትብብር አመስግነው ለሴት መምህራኖቻችን ይህን የስልጠና እድል ማግኘት በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን ለሚሰጡ ስልጠናዎች የአቅም ግንባታ ግብዓት እንደሚሆን ገልፀው ሰልጣኞች ያገኙትን ወርቃማ እድል በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል፡፡


ስልጠናው ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በስልጠናው ላይ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ 20 ሴት መምህራን እየተሳተፉ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

Share This News

Comment