Logo
News Photo

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን የሚሰጡ አሰልጣኞች ተመረቁ፡፡

በኢትዮጽያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ስርዓትን ለመጀመር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

ይህ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የዲጂታል የትምህርት ስርዓትን ለመዘርጋት ተግባረዊ እየተደረገ ያለው ፕሮጀክት (e-SHE) /e-Learning for Strengthening Higher Education / ይሰኛል፡፡

ፕሮጀክቱም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን/Mastercard Foundation፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ ከሻያሾኔ እና ከ50ዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) በትብብር ተግባራዊ እያደረጉት ሲሆን በዛሬው እለትም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ላለፋት 8 ወራት የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን የወሰዱ መምህራን ተመረቀዋል፡፡


እነዚህ የዲጂታል ትምህርት ለመስጠት ስልጠና የወሰዱት መምህራን ከተለያዩ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ሲሆኑ በቀጣይ ወደ የትምህርት ተቋማቸው በመሄድ ለሌሎች መምህራን ያገኙትን አውቀት እንዲያካፍሉ ይደረጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የዲጂታል ትምህርት ሥርዓትን መዘርጋትና ሞዴል የዲጂታል ኮርሶችን ለማዘጋጀት የሰለጠኑ መምህራን ተመራቂ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡


Share This News

Comment